‹እናት ነሽ›› የተሰኘው (የራሱ ድርሰት ነው) በ1977ዓ.ም ከወጋየኹ ንጋቱ ጋር በወለጋ ነጆ ውስጥ ሲጫወቱ፡ በቀድሞ ጊዜ ለሙዚቀኞች ብቻ ይሰጥ የሚመስልን ሽልማት ከተመልካች መካከል በየደረታቸው ተሸጉጦላቸዋል፤ ይኸንኑ ቴአትር በ ‹በበቃ› ሲያሳዩ ደግሞ ከተመልቾቹ ውስጥ አንዱ መድረክ ወጥቶ ሕዝቡንም፡ ወጋየኹና እርሱንም ‹ጓዶች አንዴ ዝም በሉ› ብሎ አስቆሞአቸው ለሚመለከተው ሰው ‹‹እባካችኹ ኪስና መሀረባችኹ ያፈራውን ጣል ጣል አርጉላቸው›› ተብሎም ተለምኖላቸዋል፤ (ሰውነታቸው ክሱ ስለነበር በትክክልም በድርቁ የተጎዱ መስሎት ነበር)፤

ከተወለደበት ጎጃም ደጀን ወረዳ ድባብሲት ማርያም በ7 ዓመቱ ወጥቶ በ1972ዓ.ም አ/አ/ዩ የቴአትር ት/ቤት ገብቶ እስከሚማርበት ጊዜ በጅማ አጋሮ ኖሯል፤ በሀገር ፍቅር ቴአትር ለ 18/19 ዓመት ያህል፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 13 ዓመታት ሠርቷል አሁንም በመስራት ላይ ይገኛል፤ በትውፊታዊ ቴአትሮች ጥናት ይታወቃል፤ መኤኒት ብሔረሰብ ላይ የጻፈው ቴአትር በቅርብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይታያል፤ በጠቅላላው 80 ያህል ድርሰቶችን ጽፏል፤
ተከታታይ ተቴሌቪዥን ፊልም ዘርፍን የሸለመልን ታላቁ የጥበብ ሰው ጸሃፌ ተውኔት አስታጥቃቸው ይሁኔ፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here